ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ የምግብ ሥርዓቶችን ማሳደግ

የኢግናይት የአየር ንብረት ፈጠራ ውድድር

የIGNITE የአየር ንብረት ፈጠራ ውድድር በአማራ እና አፋር ክልሎች የምግብ ዋስትናን፣ የግብርና ዘላቂነትን እና የአየር ንብረት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ስራ-ፈጣሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን ይፈልጋል።

ስለ ጥሪው

የአየር ንብረት + ምግብ

ከዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) እና ከCARE Denmark ጋር በመተባበር የተቋቋመው ኢግናይት የፈጠራ ውድድር በምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና የአመጋገብ ችግሮች ላይ ለመስራት የተመሰረተ በአይነቱ የመጀመሪያው ማዕከል ነው። ዋና አላማው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር እና በአካባቢው ማኅበረሰቦች የሚመራ አካታች እና ዘላቂ የምግብ ሥርዓቶችን መፍጠር ሲሆን፤ ማዕከሉ የአካባቢው ማህበረሰብ ችግሮችን ለመፍታት፣ ስራ ፈጣሪለማጎልበት እና ተጽኖውን ለማስፋት ቁርጠኛ ነው።

ማዕከሉ ከWFP Ethiopia Office፣ CARE Ethiopia እንዲሁም ከIceaddis ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የፈጠራ ውድድር ፕሮግራም እያስጀመረ ነው። የመርሃ ግብሩ አላማ በምግብ ምርትና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ችግሮችን መፍታት የሚችሉ ስራ ፈጣሪዎችን ማበረታታት ነው።

ተባባሪዎች

ትኩረት

የኢግናይት የአየር ንብረት ፈጠራ ውድድር በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ የተጋላጭ ማኅበረሰቦችን ልዩ ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ አሰራሮችን እንዲዳብሩ በማበረታታት፣ መፍትሄዎችን ለማምጣት ያለመ መርሃ ግብር ነው።

ይህ ውጥን የአየር ንብረት ለውጥ በምግብ ዋስትና እና በግብርና ላይ የሚያስከትለውን ተፅእኖ በመቅረፍ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ ይፈልጋል።

መርሃ ግብሩ ስራ ፈጣሪዎች ሀሳባቸውን የሚያሳዩበት፣ ድጋፍ የሚያገኙበት እና ፈጠራዎቻቸውን የሚያጎሉበት መድረክ በማቅረብ፣ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለአየር ንብረት ችግሮች ውጤታማ መፍትሄዎች ላይ ለመድረስ ይሰራል።

1. ገበያ እና ፍጆታ

የተመጣጠነ የምግብ ፍላጎትንና የሸቀጦች ግብይትን የሚያነቃቁ አዳዲስ ፈጠራዎች፣

ዘላቂ እንቅስቃሴዎች ላይ በማተኮር የተጠቃሚዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ያለሙ መፍትሄዎች።

2. ከአየር ንብረቱ

ጋር የሚስማማ

ግብርና

ለእንስሳት ምርት አያያዝ፣ ማቀነባበር እና የግብይት የፀሐይ/ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣

የግብርና ምርታማነትን እና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮች መጠቀም፣

በዲጂታል ላይ የተመሰረተ የበሽታ ምርመራ እና የሰነድ አያያዝ ዘዴዎችን ማዳበር፣

በሽታን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን እና ዘመናዊ የግብርና ቴክኒኮችን ማዳበር።

 3. የውሃ ሃብት

ፈጠራዎች

ቀልጣፋ የውሃ ሀብት አያያዘና አጠቃቀምን የሚያረጋግጡ አዳዲስ ፈጠራዎች፣

በግብርና አውድ ውስጥ የውሃ እጥረት፣ ጥራትና ተደራሽነት ችግሮችን የሚቀርፉ መፍትሄዎች።

መርሐግብር

  • የማስረከቢያ ቀነ-ገደብነሐሴ 6፣ 2016 ዓ.ም

    የኢግናይት ፈጠራ ውድድር ማመልከቻ የማስረከቢያ ቀነ-ገደብ ነሐሴ 6፣ 2016 ዓ.ም ነው።
    ማመልከቻዎች በ http://iceaddis.com/ignitehubet-am ላይ በተጠቀሰው ቅጽ ወይም በአገር ውስጥ ባሉ የዓለም ምግብ ፕሮግራም እና CARE ቢሮዎች ሊቀርቡ ይችላሉ። አመልካቾች ቅጹን ወስደው ለተመረጡ (የአማራ እና የአፋር) ክልል ቢሮዎች ማቅረብ ይችላሉ። ማመልከቻዎቹ አስፈላጊ ዝርዝር መረጃዎችን በቅጹ ማካተት አለባቸው።
    የምርጫ መስፈርት፡-
    ● ፈጠራ፡- የታቀደው የመፍትሄ ሃሳብ ነባር ጉድለቶችን የመሙላት አቅሙን ጨምሮ፣ የፈጠራው ደረጃ እና ልዩነት ይገመገማል።
    ● ተፅዕኖ፡- መፍትሔው በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ እና በተጠቀሱት ክልሎች ውስጥ ያሉ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ይገመገማል።
    ● አዋጭነት፡- የቀረበውን የመፍትሄ ሃሳብ የአተገባበር እንዲሁም ቴክኒካል አዋጭነቱን ጨምሮ መጠነ ሰፊነቱን እና የረዥም ጊዜ ዘላቂነቱ ይገመገማል።
    ● ከዓላማዎች ጋር መጣጣም፡ አተገባበሩ ከኢግናይት ፈጠራ ውድድር ግቦች እና አላማዎች ጋር እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ የምግብ ስርዓትን የማጎልበት አጠቃላይ ተልእኮውን ለማሳካት ካለው አቅም ጋር መጣጣሙ ይገመገማል።
    ● የአካባቢ አውድ፡ ሃሳቡ ምን ያህል የአካባቢ ሁኔታዎችን፣ ባህሎችን፣ ፍላጎቶችን እና የአካባቢ ችግሮችን ለመፍታት መፍትሄዎችን የመጠቀም ችሎታን ያሳያል የሚለው ይገመገማል።
  • ቋንቋየማመልከቻ ቋንቋዎች

    አመልካቾች ማመልከቻቸውን በእንግሊዝኛ ወይም በአማርኛ ማቅረብ ይችላሉ።
  • ልዩ ድንጋጌዎች

    የቀረቡት ተወዳዳሪ ፕሮጀክቶች ለዳኞች ከመቅረባቸው በፊት መስፈርቱን የሚያሟሉ መሆናቸው ይጣራል።
    በቴክኒክ ችግሮች ምክንያት ዘግይተው ለሚቀርቡት ማመልከቻዎች አጋሮች ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም።

አጋሮች

ለፈጠራ ማዕከሉ ድጋፍ ስለሰጡን አጋሮቻችን ትልቅ ምስጋና እናቀርባለን።

ያግኙን

ማንኛውም ጥያቄዎች ወይም እርዳታ ይፈልጋሉ? በኢ-ምይል፡ apply@iceaddis.com ወይም ስልክ ቁጥር፡ +25191042 9775

ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ሰነዶች ያውርዱ፡-

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያግኙን

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እኛን በመከተል በሁሉም የክስተት ዜናዎች እና ማስታወቂያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ።